እንኳን #ለቅዱስ_መርትያኖስ_ኤጲስ_ቆጶስ እና #ለቅዱስ_ዮሐንስ_ጻድቅ_ዘደብረ_ቢዘን፣ #ለቅዱስ_ጻድቅ_ዳንኤል_ገዳማዊ ለሌሎቹም ንዑዳን ክቡራን ክብረ በዓላት በሰላም አደረሳችሁ።
በዲያቆን መልአኩ ይፍሩ
----------------------------------------------------------------
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
¶ አመ ፲፬ ለኅዳር በዛቲ ዕለት፥ አዕረፈ አብ #ቅዱስ_አባ_መርትያኖስ ኤጲስ ቆጶስ ዘሀገረ ጠራክያ።
✍️፩-ኅዳር ፲፬ በዚህች ዕለት የጠራክያ አገር ኤጲስ ቆጶስ #ቅዱስ_አባ_መርትያኖስ አረፈ።
+ ይህም ቅዱስ ሶርያ በምትባል አገር የተወለደ ሲኾን ወላጆቹም ክርስቲያን ናቸው። እርሱም በገድል የተጠመደ ተጋዳይ ነው። አርዮሳውያንንም በክህደታቸው ምክንያት የሚያወግዛቸውና የሚያሳድዳቸው ኾነ። እነርሱም እነርሱም በርሱ ላይ ልዩ ልዩ መከራ ያደርሱበትና በሚያልፍበትም ጎዳና ጠብቀው ይዘውም ሜዳ ላይ እየጎተቱ ያሠቃዩት ይደበድቡትም ነበር። እነርሱም አሳደዱትና ተሰዶ ሸሽቶ ወደ ኤርትራ ባሕር ዳር መጥቶ በዚያ ከምድር የሚበቅሉትን ቅጠሎች እየተመገበ በዋሻ ተወስኖ ለብዙ ዓመታት ኖረ።
+ ቸሩ እግዚብሔርም ለኤጲስ ቆጶስነት መረጠውና ይህ ጽኑዕ ተጋድሎው በአገሩ ሲሰማ ይዘው ወሰዱና ጠራክያ በምትባል አገር ላይ ኤጲስ ቆጶስነት ሾሙት። እርሱም እግዚአብሔርን ደስ በሚያሰኘው በጎ ምግባር ተጓዘ። በርሱም የኤጲስ ቆጶስነት ዘመን በብዙዎች ላይ ሰላም ፍቅር አንድነትም ኾነ። ቸሩ እግዚአብሔርም በዚህ ቅዱስ አባት እጆች ብዙ ድንቆች ተአምራትን አድርጓል። ከነዚህም አንዱ ሰዎች ውንድ ሰው ሙቶባቸው ይዘው ሊቀብሩ ሲኼዱ አንድ ክፉ ሰው ከመንገድ ቆይቶ ዕዳ አለበትና አትወስዱትም አላቸው። ቅዱሱ አባታችን ብዙ ቢለምነውም ሊሰማ አልቻለም። በመጨረሻም አባ መርትያኖስ ወደ ሰማይ ዐይኖቹን አቅንቶ ቢጸልይ ያ የሞተ ሰው አፈፍ ብሎ ተነሳና ምንም ምን ዕዳ እንደሌለበት መሰከረ። አባ መርትያኖስም ልጄ ስለምን በሐሰት ተናገርህ? ኹሉም የሚመረምረውን ቸሩን እግዚአብሔርን አትፈራውምን አለው። ከዚያም ያ ዓመፀኛ ሰው ሞተና ያ ሙቶ ሊቀ'በር የነበረው ሰው ግን ከሞት ተነስዮ በሰላም ወደቤቱ ኼደ። ከዚህም በኋላ ቅዱስ መርትያኖስ ብዙ ዘመናትን ኖረ፣ መልካም፡አገልግሎቱንም ፈጽሞ በሰላም አረፈ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን፣ እኛንም በቅዱስ መርትያኖስ ጸሎት ይማረን፣ በረከቱም በእኛ ላይ እጽፍ ኹና ትደርብን ለዘላለሙ አሜን።
ሰላም ለመርትያኖስ ምሉአ ጸጋ ወሀብት
ከመ ይስብክ ሃይማኖተ በመጣርያ እንተ ተውህበቶ ሢመት
እመርዮሳውያን ሕዝብ ሶበ ረከቦ ስደት
ኀበ ሖረ ወፈለሰ ውስተ ምድር ርኅቅት
በኃይለ ጸሎቱ ተንሥአ ምውት።
✍️፪-ዳግመኛም በዚህች ዕለት ለፋርስ ንጉሥ ተአምራትን ያደረገና ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያዳመነው #የአባ_ዳንኤል የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው።
+ ይህም የኾነው እንዲህ ነው። የፋርስይ ንጉሥ በጽኑዕ የሆድ በሽታ ይያዝና ብዙ ባለ መድኃኒቶች ጋር ቢደክማ ቢታገልም አልሆነለትም። ንጉሡም ከማዕዱ ከፍሎ የሚያበላው አንድ ሥራይኛ ነበረው። ያንንም ሥራይና እኔ ከምበላው አብልቼ ከምጠጣው አጠጥቼ የማኖርህ እንዲህ ካለው ችግር የማታድነኝ ከኾነማ ምን ሊበጀኝ አለው። ያም ሥራይኛ በተንኮል ንጉሡን እንዲህ አለው። አንድ ልጅ ብቻ ያላቸውን ሰዎች በገንዘብ ልጃቸውን ግዛቸውና አምጥተህ እናቱ አጥብቃ ትሠረው፣ አባቱም ይረደውና በሱ ደም ትድናለሁ አለው። ይህንም ማለቱ ንጉሥ ነውና ፈርቶ ምንም አያደርግም ብሎ ነው፣ ነገር ግን ንጉሡ ለወታደሮቹ ገንዘብ ሰጥቶ እንዲፈልጉ ላካቸው፣ ኋላም አንድ ባልና ሚስት ድኆች የኾኑ አገኙና አመጧቸው። እኒያም ድኆች ባልና ሚስት በፍቅረ ንዋይ ታለሉና ለልጃቸው ምንም ሳይሳሱ እናቱ አጥብቃ አሥራ ያዘችው። አባቱም ሊያርደው ሾተሉን አነሳ። ሕጻኑም ማንም የሚያድነውን ባጣ ጊዜ ዐይኖቹን ወደላይ አቅንቶ እግዚአብሔር እንዲያድነው ይማጸን ጀመረ። አምላካችንም የንጉሡን ልብ አራራለትና ፈትታችሁ ልቀቁት አለና ለቀቀው። አስቀርቦም ምን እያልህ ነበር የምትጸልየው አለው። እርሱም እናትና አባቴም ኹሉም የሚያድነኝን ባጣ ዐይኖቼን አቅንቼ ሰማያዊውን አምላኬን እንዲያድነኝ ነው የተማጸንሁት አለው።
+ ቸሩ አምላካችንም ለዚህ የንጉሡ ውለታ ወደ በጎ መንገድ ሊመልሰው ወደደና ታላቁን መነኰስ ቅዱስ አባ ዳንኤልን ወደ ንጉሡ ሰደደው። አባ ዳንኤልም መጥቶ በንጉሡ ፊት ድንቅ የኾኑ ተአምራትን አደረገ፣ ንጉሡንም ፈወሰውና የቀናቸውን የእውነት መንገድ አስተማረውና በክብር ባለቤት ኢየሱስ ክርስቶስ አሳመነውና አጠመቀው። ከዚህም በኋላ ወደ በዓቱ ተመልሲ እየተጋደለ ኖረ፣ እግዚአብሔርንም አገልግሎ በሰላም አረፈ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን፣ እኛንም በአባ ዳንኤል ጸሎይ ይማረን፣ በረከቱም በዝታ ትደርብን ለዘላለሙ አሜን።
ሰላም እብል ለዳንኤል መነኰስ
እንተ ወሀቦ ፈውሰ ለንጉሠ ፋርስ
ድኅረ እመጥባሕት ቤዘዎ በተራኅርኆ መንፈስ
እምነ እሙ ነዳዪት ወእመቡሁ ጽኑስ
ለዘትሠየጦ በወርቅ ለሕፃን ንኡስ።
✍️፫-ዳግመኛም በዚህች ዕለት #የሱራስጦስ #የእንድራዎስ #የመብሪኖስ #የራጢና እንዲሁም ደግሞ #የጋርሴስ #የበጥላን እና የደብረ ቢዘኑም የሃይማኖት መምህር #የአባ_ዮሐንስ መታሰቢያቸው ነው። በደብረ ቀልሞን የተሠራችም ቤተ ክርስቲያን የከበረችበት ነው፣ በረከታቸውም ትድረሰን ለዘላለሙ አሜን።
ሰላም ለዮሐንስ ገሣጼ ሕዝብ አብዳን
በከሊአ ዝናም ወጠል መጠነ ሠልስቱ አዝማን
እንበይነ ዝንቱ ኃይልከ ኃይለ አጥናን
ትትሜሰል በኤልያስ ወበዮሐንስ ካህን
ወበቴስባን ትትሜሰል ቢዘን።
(ምንጭ፥ ስንክሣር ዘወርኃ ኅዳር)
----------------------------------------------------------------
ወልደ ዳዊት ወልደ አብርሃም ኢየሱስ ክርስቶስ ወልደ እግዚአብሔር ሕያው በእንተ ቅዱስ መርትያኖስ ኤጲስ ቆጶስ ወቅዱስ ዳንኤል ገዳማዊ መስተጋድል ወቅዱስ ዮሐንስ መምህር ዘደብረ ቢዘን ወበእንተ ኲሎሙ ቅዱሳን እለኮነ ተዝካረ በዓሎሙ በይእቲ እለት መሐረነ ለነ ለአባስያን አግብርቲከ ወአእማቲከ አሜን።
እግዚኦ ተዘከር ኪዳን ዘወሀብኮሙ ለቅዱሳን አግብርቲከ ወአእማቲከ እለ አስመሩ ኪያከ፣ ወሶበ ተዘከርከ ዘንተ ተዘከር ከመ መሬት ንሕነ አባስያን አግብርቲከ ወአእማቲከ፣ ኢታርእየነ ሙስናሃ ለቅድስት ሀገሪትነ ኢትዮጵያ ወለቅድስት ቤተ ክርስቲያን። ኢታጥፍአነ ተዘኪረከ ዘትካት፣ ፍጡነ ይርከበነ ሳህልከ እግዚኦ።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር አሜን።
t.me @deaconmelakuyifru
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ