ማክሰኞ 17 ኖቬምበር 2020

የኅዳር ፱ ዝክረ ቅዱሳን።

እንኳን #ለጉባኤ_ኒቅያ #ለቅዱስ_ይስሐቅ_ሊቀ_ጳጳሳት እና ለሌሎቹም ንዑዳን ክቡራን ክብረ በዓላት በሰላም አደረሳችሁ።

የኅዳር ፱ ዝክረ ቅዱሳን። 

በዲያቆን መልአኩ ይፍሩ
----------------------------------------------------------------

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

¶ አመ ፱ ለኅዳር በዛቲ ዕለት፥ አዕረፈ አብ #ቅዱስ_ይስሐቅ ሊቀ ጳጳሳት ዘእስክንድርያ።

✍️፩-ኅዳር ፱ በዚህች ዕለት የእስክንድርያው አገር አርባ አንደኛው #ሊቀ_ጳጳሳት_ቅዱስ_ይስሀቅ አረፈ።

  + እህም ቅዱስ ቡርልስ ከሚባል አገር ነው። ወላጆቹም እግዚአብሔርን የሚፈሩ ባለጸጎች ናቸው። ይህንም ቅዱስ ከወለዱት በኋላ ኤጲስ ቆጶሱ ሲያጠምቀው በሕፃኑ ራስ ላይ የብርሃን መስቀል ምልክት አየ፣ ስለርሱም በቤተ ክርስቶያን ታላቅ ሹመትን እንደሚሾም ትምቢት ተናገረለት። ኋላም ጥቂት እንዳደገ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርትና ጽፈትን አስተማሩት። የቅዱሳንንም ዜና ሕይወት የሚያነብ ኾነ። ከዚያም ወደ አስቄጥስ ገዳም ገባና ከአበ ምኔቱ ከአባ ዘካርያስም መነኰሰና በገድል ተጸመደ።

  + በሌላም ጊዜ አንድ ጻድቅ ሰው ይህን ቅዱስ ይስሐቅን በቤተ ክርስቲያን አየውና በቤተ ክርስቲያን ላይ ታላቅ ሹመትን እንደሚሾም ተነበየ። በዚያም ወራት ሊቀ ጳጳሳቱ አባ ዮሐንስ ጸሕውፊ ፈለገና ቅዱስ ይስሐቅን አስመጣው። ቅዱስ ይስሐቅ ግን ወደ ገዳም መመለስ ይሻ ነበርና ጽሑፉን አበላሸው። ሊቀ ጳጳሳቱም ከርሱ ሊለየው ወዶ እንዲህ እንዳለ ያውቃልና እንደማይተወው ነገረው። ይህን ባወቀ ጊዜ ቅዱስ ይስሐቅም በሚገባ አሳምሮ ጻፈ። አባ ዮሐንስም በርሱ ደስ ተሰኘበት። ከርሱ በኋላም ስለሚሾመው ሊቀ ጳጳሳት ወደ እግዚአብሔር ቢያመለክት አባ ይስሐቅ እንደተካው ተነገረው። ይህንም ለሕዝቡ ኹሉ ነገራቸው። በኋላም አባ ዮሐንስ ልክ እምዳረፈ በርሱ ፈንታ ቅዱስ ይስሐቅን ሾሙት። በርሱም የጵጵስና ዘመን ቤተ ክርስቲያን እንደማኅቶት አበራች። በማርቆስም፡ወንበር  ሰባት ዓመት ተኩል ሲኖር እግዚአብሔርን በበጎ አገልግሎ በሰላም አረፈ። እርሱም ብዙ መከራዎችን ታግሦ ተቀብሏል። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን፣ እኛንም በቅዱስ ይስሐቅ ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ አሜን።

✍️፪-ዳግመኛም በዚህች ዕለት #የሦስት_መቶ_ዐሥራ_ስምንቱ ኤጲስ ቆጶሳት በኒቅያ የተሰበሰቡበት ነው።

ሰላም ለጳጳሳት እለስኖሙ አብርሀ
በሀገረ ኒቅያ ወአድያሚሃ
አፍራሰ ሕይወት እሉ በብሂል ዕንቋዕ ዘበፍስሓ
ዘኬዱ ውስተ ባሕር ወዘወረዱ
እንዘ የሐምጉ ማያተ ብዙኀ።
 
(ምንጭ፥ ስንክሣር ዘወርኃ ኅዳር)
----------------------------------------------------------------
ወልደ ዳዊት ወልደ አብርሃም ኢየሱስ ክርስቶስ ወልደ እግዚአብሔር ሕያው በእንተ ቅዱሳን ሠለስቱ ምዕት ዐሠርቱ ወሰምንቱ ርቱዓነ ሃይማኖት፣ ወበእንተ ቅዱስ ይስሐቅ ወበእንተ ኲሎሙ ቅዱሳን እለኮነ ተዝካረ በዓሎሙ በይእቲ እለት መሐረነ ለነ ለአባስያን አግብርቲከ ወአእማቲከ አሜን። 

እግዚኦ ተዘከር ኪዳን ዘወሀብኮሙ ለቅዱሳን አግብርቲከ ወአእማቲከ እለ አስመሩ ኪያከ፣ ወሶበ ተዘከርከ ዘንተ ተዘከር ከመ መሬት ንሕነ አባስያን አግብርቲከ ወአእማቲከ፣ ኢታርእየነ ሙስናሃ ለቅድስት ሀገሪትነ ኢትዮጵያ ወለቅድስት ቤተ ክርስቲያን።  ኢታጥፍአነ ተዘኪረከ ዘትካት፣ ፍጡነ ይርከበነ ሳህልከ እግዚኦ።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር አሜን።

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ