ዓርብ 13 ኖቬምበር 2020

+ በቅዱስ የተጻፈ የቅዱስ ገድል +

የምንኩስና ሕይወት ፋና ወጊ : የብዙ ብሒላት ተጠቃሽ : የበረሃው ኮከብ ቅዱስ እንጦንስ በምንኩስና የዘር ሐረግ ቀዳሚ ቢሆንም በሚገባው ልክ ያልተዘከረ የቤተ ክርስቲያን መብራት ነው:: በሀገራችን የመንበረ ፓትርያርክ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አስቀድሞ በስሙ የታነጸ ቤተ ክርስቲያን እንደነበረና በኁዋላ የእመቤታችን ስም እንደ ጎላም ታሪክ ያስረዳናል:: 

የቅዱስ እንጦንስ ታሪክ ወንድማችን ዲያቆን መልአኩ ይፍሩ Melaku Yifru Zewulude Birhan ተርጉሞ አቅርቦልናል:: የመጽሐፉ ጸሐፊ ራሱም ሌላ ብዙ ገድል ያለው  የኢትዮጵያዊያን የቆብ አባታችን ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ ነው:: ቅዱስ አትናቴዎስ በዘመኑ እንደ ቅዱስ እንጦንስ ያሉ አበውንና እንደ ቅድስት ሲንቀለጢቃ ያሉ እማትን ገድላት በመጻፍ ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ዕረፍት የለሽ ምርጥ ዕቃዋ መሆኑን አሳይቶአል:: ይህንን ጥንታዊ ተጠቃሽ መጽሐፍ ወንድማችን ደክሞ አበርክቶልናል:: ገዝተን ተሳልመን እናንብብ!

From: ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ