ዓርብ 13 ኖቬምበር 2020

የኅዳር ፭ ዝክረ ቅዱሳን።

እንኳን #ለቅዱስ_ለንጊኖስ_ሰማዕት እና #ለቅዱስ_ተባ_ዮሐኒ_ጻድቅ፣ ለሌሎቹም ንዑዳን ክቡራን ክብረ በዓላት በሰላም አደረሳችሁ።

የኅዳር ፭ ዝክረ ቅዱሳን። 

በዲያቆን መልአኩ ይፍሩ
----------------------------------------------------------------

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

¶ አመ ፭ ለኅዳር በዛቲ ዕለት፥ ኮነ አስተርእዮተ ርእሱ #ለቅዱስ_ለንጊኖስ ዘረገዘ ገቦሁ ለእግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ሎቱ ስብሐት እንዘ ቊሱል ዲበ ዕፀ መስቀል።

✍️፩-ኅዳር ፭ በዚህች ዕለት ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዕንጨት መስቀል ላይ ተሰቅሎ ሳለ ጐኑን የወጋ #የቅዱስ_ለንጊኖስ ራሱን የታየችበት ነው።

  + ይህም ቅዱስ በጌታችን ከአመነ በኋላ በቀጰዶቅያ አገር የጌታችንን ወንጌል በማስተማር ብዙዎችን ወደ ቀናች ሃይማኖት መለሰ። በዚህም ግብሩ የቀኑ ክፉዎች አይሁድና አረማውያን ተነሡበት። በሐሰትም ወንጅለው በቀጰዶቅያ ራሱን አስቆረጡት። ራሱንም ብቻ ቆርጠው ወደ ኢየሩሳሌም አመጡ። ኋላም ከከተማ ውጪ አውጥተው ከአንድ ተራራ ላይ ቀበሩት። 

  + ከብዙም ቀናት በኋላ እንዲህ ኾነ። አንዲት በቅዱስ ለንጊኖስ ስብከት ያመነች ሴት በቀጰዶቅያ ትኖር ነበረች። ቅዱሱም ራሱን ከተቆረጠባት እለት አንስታ ስለርሱ እጅግ እያዘነች ታለቅስ ነበር። የእግዚአብሔርም ተአምር ሊገለጥ ስለወደደ ዐይኖቿ ታወሩ። ልጇም ይዞ እየመራት ወደ ኢየሩሳሌም፣ የጌራችንን መካናት ለመሳለምና ለመዳን ነበር። ኢየሩሳሌም እንደደረሰች ግን ልጇም ሞተና በሐዘን ላይ ጽኑዕ ሐዘን ደርሶባታልና እጅግ አዘነች። በዚህም ሐዘን ሳለች እንቅልፍ መጥቷት ተነኛች፣ በሕልሟም ቅዱስ ለንጊኖስንና ልጇን አየቻቸው። ቅዱስ ለንጊኖስም ሥጋውን ከዚያ ቦታ እንድታወጣ ነገራት። ከእንቅልፏም በነቃች ጊዜ ስለቦያው ጠየቀችና አገኘቸው። ቦታውም ሲቆፈር እጅግ ጥዑም የሽቱ መዓዛ ሸተተ። የቅዱስ ለንጊኖስን እና የልጇን ሥጋ ወደ አገሯ ወሰደቻቸው። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን፣ እኛንም በዚህ ጻድቅ ጸሎት ይማረን፣ ለዘላለሙ አሜን።

ሰላም ለለንጊኖስ ዘተተክለ በሮም
ወተቀብረ ውስተ ወግር ዘኢየሩሳሌም
እንዘ ምስሌሁ ኅቡረ ወልዳ ንዉም
ከመ ተናገረ ለብእሲት በሕልም
ምስለ ጼና ዕፍረት ርእሱ አስተርአየት ዮም።

✍️፪-ዳግመኛም በዚህች ዕለት #የሰማዕት_ጢሞቴዎስ መታሰቢያው ነው፣ የሠራዊት አለቃ #ቅዱስ_ቴዎድሮስም ከሀገረ አትሪብ ወደ ሀገረ አስዩጥ ሥጋው የፈለሰበት ቤተ ክርስቲያኑም የከበረችበት ነው።

✍️፫-ዳግመኛም በዚህች ዕለት ወደ ብሔረ ሕያዋን የገባ #የአባ_ዮሐኒ መታሰቢያው ነው።

ሰላም ለከ ጢሞቴዎስ ቡሩክ
ሰማዕተ አምላክ
ብእሲ ሰማያዊ ወምድራዊ መልአክ
ኅብአኒ በክነፊከ በዕለተ ምንዳቤ ወሀውክ
እምነ ልሳን ምዑክ ወእምዐይን ድሩክ።

ሰላም ለፍልሰተ ሥጋከ ቴዎድሮስብማር
አመ ኃሙሱ ለወርኃ ኅዳር
ሶበ በማዕበላ ፈቀደት አጥፍኦታ ለምድር
ሰሚዓ ትእዛዘከ ፈለሰት ባሕር
ቃለ እግዚኡ ከመ ይሰምዕ ገብር።

ሰላም እብል ለዘኮነ ሱቱፈ
ምስለ እለ ገብሩ ሰብእ ብሔረ ሕያዋን ምዕራፈ
እምሥርዓተ መላእክት ዮሐኒ ምንተኒ ኢያትረፈ
ከመ ሕይወቶሙ ሕይወተ ተጸገወ ዘልፈ
ወከመ ክንፎሙ አብቈለ አክናፈ።

(ምንጭ፥ ስንክሣር ዘወርኃ ኅዳር)
----------------------------------------------------------------
ወልደ ዳዊት ወልደ አብርሃም ኢየሱስ ክርስቶስ ወልደ እግዚአብሔር ሕያው በእንተ ቅዱስ ለንጊኖስ ወበእንተ ቅዱስ ቴዎድሮስ ወቅዱስ ጢሞቴዎስ ወበእንተ ቅዱስ አባ ዮሐኒ ወበእንተ ኲሎሙ ቅዱሳን እለኮነ ተዝካረ በዓሎሙ በይእቲ እለት መሐረነ ለነ ለአባስያን አግብርቲከ ወአእማቲከ አሜን። 

እግዚኦ ተዘከር ኪዳን ዘወሀብኮሙ ለቅዱሳን አግብርቲከ ወአእማቲከ እለ አስመሩ ኪያከ፣ ወሶበ ተዘከርከ ዘንተ ተዘከር ከመ መሬት ንሕነ አባስያን አግብርቲከ ወአእማቲከ፣ ኢታርእየነ ሙስናሃ ለቅድስት ሀገሪትነ ኢትዮጵያ ወለቅድስት ቤተ ክርስቲያን።  ኢታጥፍአነ ተዘኪረከ ዘትካት፣ ፍጡነ ይርከበነ ሳህልከ እግዚኦ።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር አሜን።

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ