ረቡዕ 18 ኖቬምበር 2020

የኅዳር ፲ ዝክረ ቅዱሳን።

እንኳን #ለቅድስት_ሶፍያና_ለደናግል_ሰማዕታት እና ለሌሎቹም ንዑዳን ክቡራን ክብረ በዓላት በሰላም አደረሳችሁ።

የኅዳር ፲ ዝክረ ቅዱሳን። 

በዲያቆን መልአኩ ይፍሩ
----------------------------------------------------------------

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

¶ አመ ፲ ለኅዳር በዛቲ ዕለት፥ ኮና ሰማዕተ #ደናግል_ቅዱሳት_መነኰሳይያት_ንጹሐት #ወእሞን_ሶፍያ።

✍️፩-ኅዳር ፲ በዚህች ዕለት #ቅዱሳት_ንጹሐት_መነኰሳይያት_ደናግል #እናታቸው_ሶፍያም በሰማዕትነት አረፉ።

  + ይህም የኾነው እሊህ ቅዱሳት ደናግል ከተለያየ አገር መለኮታዊት ፍቅር ጠራቻቸውና ተሰባስበው በሮሜ ካሉ ገዳማት በአንዱ የምንኲስናን ልብስ ለብሰው ይኖሩ ነበር። ለነርሱም ቅድስት ሶፍያ የተባለች እመምኔት ነበረቻቸው። እርሷም በበጎ ምግባር የተሸለምውች ናትና ልክ እንደንጹሐን መላእክት እስኪኾኑ አደረሰቻቸው። ከነርሱ መኻከል አረጋውያን የኾኑ ሲኖሩ እንዲሁ ደግኖ ልጅ እግር የኾኑ ወጣቶችም አሉ። 

  + ከጊዜም በኋላ ከሀዲው ንጉሥ ዑልያኖስ ከፋርስ ንጉሥ ከሳቦር ጋራ ሊዋጋ በሮሀ በኩል ሲያልፍ በመንገድ ይህን ገዳም ይመለከትና ስለምንነቱ ይጠይቃል። የደናግል ገዳም መኾኑን በነገሩት ጊዜ ወታደሮቹን ልኮ አወደመው፣ መነኰሳይያቱንም ከቅድስት እመምኔታቸው ሶፍያ ጋራ በአንድነት የሰማዕትነትን አክሊል ተቀበሉ። ንጉሡንም ደግሞ ታላቁ ኃያል ሰማዕት ቅዱስ መርቆሬዎስ በዐፀደ ሥጋ ኼዶ በጦሩ ወግቶ ገደለው። እርሱ በሥጋ በነፍስ ሲጎዳ እሊያ ሰማዕታት ግን በነፍስ ተጠቀሙ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን፣ እኛንም በሰማዕታቱ ጸሎት ይማረን፣ በረከታቸውም እጽፍ ድርብ ኾና ትደርብን።

ሰላም ለደናግል እምተደልዎ ወእምተሐውዞ
ለወልደ ማርያም ድንግል እንዘ ይተልዋ ግዕዞ
ሶበ ዑልያኖስ ቀተሎን ለእሎን በተጋዕዞ
እግዚአብሔር መስተበቅል ለመርቆሬዎስ አዘዞ
በቀለ ደሞን በኲናት ይርግዞ።

✍️፪-ዳግመኛም በዚህች ዕለት በእስክንድርያ አገር ሊቀ ጳጳሳት በድሜጥሮስ ዘመን #ስለጾም_ሥርዓት ቅዱሳን #ሊቃነ_ጳጳሳት_የአንድነት_ስብሰባ አደረጉ።

  + ይህም የኾነው ቀድሞ የጌታችን በዓላትና አጽዋማት ያለ ቀመር እንዲሁ በዋለበት ቀን ነበር የሚከበረው። በኋላ ግን በእስክንድርያ ይህ ቅዱስ ድሜጥሮስ ከመጣ በኋላ ሱባኤ ገብቶ ልዩ የኾነውን የባሕረ ሐሳብን ቀመር ቀምሮ አሰናዳ። የጌታችንን አጽዋማትና በዓላት ከሠራ በኋላ ለሌሎች አገራትም ኤጲስ ቆጶሳት ላከው። እነርሱም መልእክቷን በተመለከቱ ጊዜ ደስ ተዘኙበት። 

  + የሮሜውም አገር ሊቀ ጳጳሳት አባ ፊቅጦር መልእክቱ እንደደረሰው ተመልክቷት ደስ ተሰኘባት። ለአንጾኪያውም ሊቀ ጳጳሳት አባ መክሲሞስ ላከ። ወደ ኢየሩሳሌሙም ሊቀ ጳጳሳት ወደ አባ አጋብዮስ ላከ። እነርሱም ኹላቸው ባነቡት ጊዜ ደስ ተሰኙባቸው። የሮሜው ሊቀ ጳጳሳት አባ ፊቅጦርም በሮሜ ያሉትን ኹሉ ኤጲስ ቆጶሳት ስብሰባ ጠርቶ በሊቃውንቱ ኹሉ ፊት አነበቧት። ደስም ተሰኙባትና የአጽዋማትና የበዓላትን ነገር በርሷ ለማስተካካል። ለግዚአብሔር ምስጋና ይሁን፣ እኛንም በጸሎታቸው ይማረን ለዘላለሙ አሜን።

ሰላም ለክሙ ካህናተ ስባሔ ወዘምሮ
ዘአፍጠንክሙ ሐዊረ እንበለ ተድኅሮ
ውስተ አሐዱ መካን ለተጋብኦ ወለአማኅብሮ
ሐሳበ አበቅቴ ዘመንፈስ ቅዱስ መሀሮ 
እምነ ድሜጥሮስ አብ ትንስኡ አእምሮ።

✍️፫-ዳግመኛም በዚህች ዕለት  #የጳውሎስና #የሦስት_ሰማዕታት መታሰቢያቸው ነው። በረከታቸው ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

(ምንጭ፥ ስንክሣር ዘወርኃ ኅዳር)
----------------------------------------------------------------
ወልደ ዳዊት ወልደ አብርሃም ኢየሱስ ክርስቶስ ወልደ እግዚአብሔር ሕያው በእንተ ቅድስት ሶፍያ ወቅዱሳት ደናግል መነኰሳይያት ወበእንተ ቅዱሳን ኤጲስ ቆጶሳት ወበእንተ ኲሎሙ ቅዱሳን እለኮነ ተዝካረ በዓሎሙ በይእቲ እለት መሐረነ ለነ ለአባስያን አግብርቲከ ወአእማቲከ አሜን። 

እግዚኦ ተዘከር ኪዳን ዘወሀብኮሙ ለቅዱሳን አግብርቲከ ወአእማቲከ እለ አስመሩ ኪያከ፣ ወሶበ ተዘከርከ ዘንተ ተዘከር ከመ መሬት ንሕነ አባስያን አግብርቲከ ወአእማቲከ፣ ኢታርእየነ ሙስናሃ ለቅድስት ሀገሪትነ ኢትዮጵያ ወለቅድስት ቤተ ክርስቲያን።  ኢታጥፍአነ ተዘኪረከ ዘትካት፣ ፍጡነ ይርከበነ ሳህልከ እግዚኦ።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር አሜን።

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ