"እንኪያስ እናምነው ዘንድ በቊዔት ያለ'ው የትኛው ነው? ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ኾነ እና ምንም ስለ ሰው ልጆች መዳን ባለ'ው አሳብ ምክንያት የሰብአዊ ባሕርያችንን ሥጋን ነሥቶ ቢወስድም ያ ቀድሞ በእግዚአብሔርነቱ በመለኮቱ የነበረው ባሕርዩ ኹሉ በምንም በምን መንገድ እንዳልተለወጠ፣ [መለኮት ከሰብአዊ ባሕርያችን ጋር በመዋሐዱም ሥጋን ከመለኮታዊ ባሕርዩ ሡቱፍ ያደርገው ዘንድ እንዲህ ማድረጉን] መመስከር ወይንስ አምላክን በአራዊት እና በከብቶች እንመስለው? ከዚህም በሚገኘው ነገር ምክንያት ሰው ራሱን ልክ እንደ አራዊት እና እንደ ምድር ተሳቢ እንስሳት ምሳሌ በማድረግ እነርሱን ያምልክን?"
#ማኅቶተ_ገዳም ገጽ 119 -120
(ቅዱስ እንጦንስ ሊፈትኑት ለመጡ የግሪክ ዕውቅ ፈላስፎች ከሰጠው መልስ)
"ጾምን ቸል አትበሏት፤ የክርስቶስን የሕይወት መንገድ የምትደነግግ (መሠረት) ናትና።"
ጾሙን ለድኅነትና ለሰላም ለበጎ ዋጋ ኹሉ ያድርግልን።
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ