+ + + + + + + + + + + + + ++ ++++++
❤️. ❤️. ❤️. ❤️. ❤️. ❤️. ❤️. ❤️
የመላእክት አለቃ #ከሣቴ ምስጢራት ቅዱስ ዑራኤል በዛሬው እለት በሚነበበው ድርሳኑ፣
❤️ የኢየሩሳሌምን ጥፋት እዳያይ ተመኝቶ ጸሎቱም ተሰምቶለት ለ፸ ዘመን ስለተኛው አባ ባሮክ ስለተባለው ዲያቆን ይነግረናል። ይህ ዲያቆን ካንቀላፋበትም ከተነሳ በኋላ ወደ ኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ በመግባት ፵ መአልት ፵ ሌሊት ከጾመ በኋላ መልአኩ ተገልጦ ምን እንደሚፈልግ ጠየቀው። ይህም ዲያቆን ወደፊት ስለሚመጡት ደጋግ እና ክፉ ስለሆኑት #ጳጳሳት እና #ነገሥታትን ነገር ማወቅ እንደሚሻ ነገረው።
+ መልአኩም ምስጢራቱን ገለጠለት። በኢትዮጵያም ስለሚገሡት ነገሥታት እንኳ ሳይቀር፣ በዘመናቸውም የሚሆነውን ገለጠለት።
+ + + + + + + + + + +
❤️ ተወዳጁ #ናዛዜ ኅዙናን፣ #ከሣቴ ምስጢራት፣ #መራሔ ብርሃናት #ሊቀ መላእክት መልአከ ሠላም ቅዱስ ዑራኤልን ባሰብሁ ጊዜ ከሚያስደንቁኝ እና ልቤን እጅግ በታላቅ፡ደስታ ከሚሞሉት ነገሮች አንዱ፣ በድርሳኑም እንደተገለጠው፣ ድርሳኑ የተደረሰው #በርኅርኅተ ሕሊና አዛኝት ወላዲተ አምላክ ማርያም #ገላጢነት በፍቊረ እግዚእ አቡቀለምሲስ በተባለ #ቊጹረ ገጽ ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ መሆኑ ነው።
❤️አንተ ቅዱስ እንዲያው ግን ምንኛ የታደልህ ነህ?! የጌታን መከራ እስከ መስቀሉ ድረስ ተገኝተህ በመካፈልህ አዛኝቷን ተቀበልህልን፣ ወንጌልህም ከወንጌላውያን ልዩ እና ድንቅ ነው፣ መልእክታትህም ልብን የሚመስጡ፣ ልቡናን ይሚያረጋጉ። ራእይህም ድንቅና ልዩ የሆነ ነው።
ጌታ የሚወደው የተባልህ ድንቅ ሐዋርያ ሆይ በእውነት ያለሐሰት ይህን ጸጋ የሰጠህ፣ ቢሰጥ ይማያልቅበት ባዕለ ጠጋ ፈጣሬ ፍጡራን ሥሉስ ቅዱስ ምንኛ ቸርና ድንቅ ነው። ላንተ እሊህን ምስጢራት ያሰጠች አዛኝቷስ ምንኛ ውድ ናት።
❤️መስቀሉ ስር ካገኘኸው አንስቶ ያልተለየህም ሊቀ መላእክት #ከሣቴ ምስጢር ቅዱስ ዑራኤልም ምንኛ ውድ ነው።
#አስተምሕር ለነ ኦ መፍቀሬ ክርስቶስ #ፍቊረ እግዚእ።
አሜን። በጽድቅ እንበለ ሐሰት ለይኩን ለይኩን።
©ዘዲያቆን መልአኩ ይፍሩ
ጥቅምት ፳፪/ ፳፻ ወ፲፩ዓ.ም
ሲቹዋን ቸንዱ፣ ቻይና
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ