በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
የቅዱስ ቆጵረስ እና የቅዱስ ፔታርፔሞቲስ ተጋድሎ
(ምንጭ፦The paradise of the holly fathers by St. Athanasius, volume 1
ትርጉም፦ ዲያቆን መልአኩ ይፍሩ ዘውሉደ ብርሃን)
...
ውድ የእግዚአብሔር ፍጡራን መድኅን ዓለም ሕይወታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በንጹሕ እና በክቡር ደሙ በውድ ዋጋ የገዛችሁ፣ የቅዱሳን ጻድቃን ወዳጆች እመ አምላክ እናት ዓለም ድንግል ማርያምን ከመስቀሉ ስር በአደራ የተቀበላችሁ እንኳን አምላከ ቅዱሳን እግዚአብሔር ከዚህች ከተባረከች እለት አደረሳችሁ። ሳነብ ካገኘሁት እና ካስደነቁኝ የቅዱሳን ተጋድሎ ጥቂት ላካፍላችሁ። ከዚህ በማስከተል የማካፍላችሁ ድንቅ የእግዚአብሔርን አጠራር እና የቅዱሳኑን ተጋድሎ የምትመለከቱበት፣ ለካ እግዚአብሔር እንዲህም ያለውን ጠርቶ ምርጥ ድንቅ የርሱ ተወዳጅ ልጅ እና ምስክር ያደርጋል የሚያስብለን ነው።
ቅዱስ አትናቴዎስ የበረሃውያን ቅዱሳንን ተገጋድሎ በከተበበት “የቅዱሳን አበው ገነት” በተባለው ባለ ሁለት ቅጽ መጽሐፉ ከዘገባቸው ታሪኮች መኻከል አንዱን ላካፍላችሁ። አምላከ ቅዱሳን በረድኤት አይለየን።
(ትረካውን የሚተርከው ቅዱስ አትናቴዎስ እንደሆነ ልብ በሉልኝ። በጎደለ፣ ቃላት ግድፈት ቢገኝ እያረማችሁ ታነቡት ዘንድ በትሕትና እጠይቃለሁ)
ቅዱስ ቆጵረስ በግብጽ በረሐ በተጋድሎ የሚኖር የሃምሳ መናንያን አበምኔት ነበር። ብዙ ድንቆችንም ያደርግ ነበር። ድዉያንን መፈወስ፤ ልዩ ልዩ በሽታዎችንም ያድን ነበር፤ አጋንንትን አስወጥቶ ይሰዳቸው፣ ክፉ መናፍስትንም ያሳድዳቸው ነበር። ከሠራቸው ድንቆች በዓይናችን ያየናቸውም ነበሩ። በተመለከተንም ጊዜ እጅግ ተደስቶ ሰላምታ ሰጠን እና ከጸለየልን በኋላ እግራችንን አጠበን። ከዚህም በማስከተል ስለዓለሙ እና ስለጓዙ ጠየቀን። እኛ ግን አስቀድሞ የርሱን ሕይወት ታሪክ እና ሥራዎቹን ያጫውተን ዘንድ ጠየቅነው። ያም በውስጡ አንዳች እንኳ መታበይ የማይገኝበት ቅዱስ ሰውም ስለራሱ እና ስለሥራው፣ ስለታላላቆቹም ቅዱሳን ይነግረን ጀመር። (እርሱንም/ቅዱስ ቆጵረስንም/ ቀደዚህ ሕይወት እንዲገባ ስላደረጉት ቅዱሳን አበው ጭምር ይነግራቸው ጀመር ) “ልጆቼ ሆይ፣ የኔስ የሕይወት ሁናቴ እና የትኅርምት ኑሮ ከቀደሙት አበው ጋር ፈጽሞ የሚወዳደር አይደለም” በማለት መለሰልን።
“ምክንያቱም ከእኔ በፊት አንድ ስሙ ፔታርፔሞቲስ የሚባል ሰው ነበር፤ እርሱም ቀዳሚው እና በዚህ ቦታ ያሉት መነኮሳት ሁሉ አባት ነው። ይህን ቦታም ለምናኔ የለየው ርሱ ነው።ቀድሞ የአሕዛብን መቃብር የሚዘርፍ እና የሚመዘብር ሌባ(ዘራፊ) የነበረ፣ በዚህም በስርቆቱ እና በዝርፊያ ሥራው ወደ ቅድስና ሕይወት እንዲገባ ምክንያት ሆነው።”
“አንድ እለትም የአንዲትን የተባረከች ሴት (መነኲሲት) በአት ሊዘርፍ ሲሄድ ሳያውቀው ራሱን ከበአቷ ጣሪያ ላይ ያገኘዋል፤ ከዚያ በኋላ ግን ወደቤቷ መግባት እና መዝረፍ ተሳነው። ምክንያቱም የቤቷ ጣሪያ እንደመሪት ለጥ ያለ(flat roof) ስለነበር ነው።(በኪነ ሕንጻ ሙያ በረሓ ላይ የሚሠሩ ቤቶች፣ በበረሓ ዝናም እጅግ ጥቂት ከመሆኑ ወይንም ካለመኖሩ የተነሳ ወለል የመሰለ ጣሪያ(flat roof) በማድረግ ቤታቸውን ይሠራሉ። ስለዚህም አንዳንዴ የዝናም ውሃ መውረጃ አሸንዳ ላይኖር ይችላል።)
(በግብጽ)፣ቲቢያ ውስጥ ያሉ ቤቶች የዝናም ውሃ የሚወርድበት አሸንዳ ስለሌላቸው ወደቤቱ የሚገባበትም ሆነ ከዚያ የሚወጣበትን መንገድ አላገኘም ነበር። ከዚያም ማምለጥ ባለመቻሉ እስከጥዋት ድረስ ቆየ።እስከጥዋትም ምን እያደረገ እንደሚቆይ እያወጣ እያወረደ ሳለ የሰመመን እንቅልፍ ያዘውና መልአከ እግዚአብሔር በሰው አምሳል ተገልጦ ‘ራስህን እንዲህ ባለው የስርቆት እና የክፋት ሕይወት ታቆይ ዘንድ ዝም ብለህ አትመልከት፤ ሕይወትህን መቀየርና መልካም ሥራን በመሥራት ለመኖር ከወደድህ ከንጉሥ ክርስቶስ ፊት እንደመላእክት መልአካዊ አገልግሎትን አገልግል፤ ስለዚህም ይህን የምታደርግበትን ኃይል እና ሥልጣን ከርሱ ታገኛለህ’ አለው።
ይህንንም ከተገለጠለት መልአክ በደስታ እና በታላቅ ሐሴት ውስጥ ሁኖ ከሰማ በኋላ መልአኩ ማኅበረ መነኮሳትን አሳየውና የነርሱ ሁሉ አባትእንደሚሆን ነገረው። ከዚህም ሁሉ በኋላ ከነበረበት የሰመመን እንቅልፍ ሲነቃ ከፊቱ አንዲት ሴት ቁማ ተመለከተ። ”
(ከዚህ በኋላ ምንይሆን ይሆን? ቅዱስ ፔታርፔሞቲስን ምን ይገጥመው ይሆን? ከፊቱ የቆመችውስ ሴት ማን ትሆን? ሴቴቱስ ምን ትለው ይሆን? ቀጣዩ የፔታርፔሞቲስ የሕይወት እጣ ምን ይሆን ይሆን?) እኒህን በቀጣይዋ ጦማር እንመለከታለን። ለዚህም ሁሉ የቅዱሳኑ ሁሉ ቃልኪዳን እና ጸሎት የቅድስት እናታችን እመአምላክ ድንግል ማርያም አማላጅነት አይለየን። ይቆየን።
©ዘዲያቆን መልአኩ ይፍሩ
ጥቅምት 20/ 2010 ዓ.ም
ጎንደር/ ኢትዮጵያ

ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ