በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
(ምንጭ፦The paradise of the holly fathers by St. Athanasius, volume 1
ትርጉም፦ ዲያቆን መልአኩ ይፍሩ ዘውሉደ ብርሃን)
(ውድ
ኦርቶዶክሳውያን ወንድሞቼ እና እኅቶቼ በተባለው እለት ባለመለጠፌ እጅግ ይቅርታ እጠይቃለሁ። ይህ የሆነው ”በኢንተርኔት” መቋረጥ ምክንያት መሆኑን እንድታውቁልኝ
እወዳለሁ። በዚህም ላይ ሌሎች ወንድሞች እና እኅቶች እንዲያነቡት
እንድትጋሩት እጠይቃለሁ። ረድኤተ እግዚአብሄር አይለየን።)
“ይህንንም ከተገለጠለት መልአክ በደስታ
እና በታላቅ ሐሴት ውስጥ ሁኖ ከሰማ በኋላ መልአኩ ማኅበረ መነኮሳትን አሳየውና የነርሱ ሁሉ አባትእንደሚሆን ነገረው። ከዚህም ሁሉ
በኋላ ከነበረበት የሰመመን እንቅልፍ ሲነቃ ከፊቱ መነኲሲቷን ቁማ ተመለከተ። እንዲህም አለችው ‘አንተ ሰው እዚህ
ምን ታደርጋለህ? ምንድነው መልስህ? ከወዴትስ ነው የመጣኸው? ማን ትባላለህ’። እርሱም ‘አላውቅም፤ ነገር ግን ቤተክርስቲያን
ያለበትን ቦታ ታሳዪኝ ዘንድ እሻለሁ’ አላት።እርሷም እንዳሳየችው ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብቶ ከአበው እግር
ሥር በመደፋት ክርስቲያን እንዲያደርጉት አጥብቆ ይማጸናቸዋል፤ የንስሐ እድል ያገኝ ዘንድ።
አበውም ማን እንደሆነ ባወቁ ጌዜ አደነቁ፤ ከዚህ በኋላ ሰዎችን የሚገድል እና የሚጎዳ
እንዳይሆን ገሠጹት። ከዚህ በኋላ መዝሙራትን ያስተምሩት ዘንድ ጠየቃቸው፤ የመጀመሪያውን መዝሙር ሦስት ቁጥሮች እንደተማረ ‘ይህን ያህል ከተማርሁ ይበቃኛል’ አላቸው።
ከእነርሱም ጋራ ለሦስት ቀናት ከቆየ በኋላ ተለያቸውና ወደ በረሐ ሄደ። በዚያም ለአምስት ሳምንታት ያለምንም ዳቦ ሲቆይ አንድ ሰው
ወደርሱ ዳቦ እና ውሃ ይዞ መጣ።(ልብ በሉ በወጣኒነት እንዲህ ያለ
ተጋድሎ፤ እንደምን ያለውን ጸጋ ቢያገኝ ይሆን?) እርሱም ከዚያ በኋላ ይበላና ራሱን ያሳርፍ ዘንድ ሰጠው።
ፔታርፔሞቲስም ከዚህ በኋላ በዚያ በረሓ በእንባ እና በጸሎት ለሦስት አመታት ኖረ፤
በዚህም ሲቆይ በበረሐ ያሉትን ሥራሥሮች እየተመገበ ነበር የኖረው። ከሦስት ዓመታት በኋላም ወደዚያ ቤተክርስቲያን ተመለሰ፤ በአበውም
ፊት የቤተ ክርስቲያንን አስተመህሮ ጠንቅቆ አውቆ ተገኘ። መልእክታትን ባይማርም እንኳን የመጽሐፍ ቅዱስን ቃላት በልቡ ይደግማቸው(ያመላልሳቸው)
ነበር።
ታላላቁም አበው ይህንበማየታቸው በርሱ ተደነቁ፤ እንደርሱ ያለ እንዴት እንዲህ ያለ
የእውቀት እና የትሕርምት ደረጃ ሊደርስ ይችላል ብለው አደነቁ። ካጠመቁትም በኋላ ከነርሱ ጋር እንዲቆይ ጠየቁት። በዚያም ከነርሱ
ጋር ለሰባት እለታት ከቆየ በኋላ ዳግመኛ ወደ በረሐ ሄደ። በዚያም ለተጨማሪ ሰባት ዓመታት ኖረ።
በዚህ የተባረከ ሰውም በየሳምንቱ እሑድ ከመንተራሻው ሥር ዳቦ ይገኝ ነበር። ጸሎት
እና ምስጋናውን ከጨረሰ በኋላ ከዚያ ተመግቦ እስከሚመጣው እሑድ ድረስ ያለምንም መሰቀቅ ይጾም ነበር።(ልብ በሉ እኛ ስንጾም እንዴት እንሰቀቃለን። በእውነት ይህስ ተጋድሎ ግሩም
ነው)
ከበረሐውም በታላቅ
የመንፈሳዊ ጥበብ እና ጸጋ ወጥቶ የራሱን የብቸኝነትና ራስን የመካድ መመሪያ ገለጠ።(ከዚህ ላይ የገዳሙን ሥርዓት መሆኑን ልብ ይሏል) ሌሎች እርሱን ይከተሉት ዘንድ ሲመጡ ይቀበላቸው ጀመር። አንድ እለትም አንድ
ሰው ወደርሱ መጥቶ የርሱ ደቀ መዝሙር ያደርገው ዘንድ ጠየቀው። ፔፓርፖሞቲስም ከተ ቀበለው በኋላ ልክ እርሱ እንደለበሰው አለበሰው።
ü አጭር እጅጌ ያለው ሸሚዝ
ü የአፍአ መጎናጸፊያ
ü ለራሱም ቆብ(cowl-እንደሠሌን ያለ) አደረገለት
ከዚያም የመነኮሳትን ሕይወት እና ሥራ ካስተማረው በኋላ በትክሻው ላይ ካባ አደረገለት።
ለዚህም ቅዱስ ሰው (ለፔታርፔሞቲስ) ልማድ እንደሚከተለው ያለ ነው።አንድ ክርስቲያን
ሲሞት ከርሱጋር ምሽቱን ሁሉ በጸሎት እና በትጋት አብሮት ያሳልፍና በመንፈሳዊ መንገድ አልብሶ (ገንዞ) ይቀብረዋል። ይህም ደቀ
መዝሙር እንዲህ ሲያደርግ በተመለከተው ጊዜ እንዲህ አለው ‘አባቴ ሆይ፣ እኔም ስሞት እንዲህ ነው የምታለብሰኝ(የምትገንዘኝ)?’
እርሱም መለሰ ‘እንዲህ ባለው ሁኔታ አለብስሃለሁ፤ ከዚያም ይበቃኛል እስክትነኝ
ድረስ በከፈን እሸፍንሃለሁ።’ ያም ደቀ መዝሙር አረፈና የፔታርፔሞቲስ ቃልም . . . ”
(ቅዱስ ፔታርፔሞቲስ ምን ያደርግ ይሆን?
ደግሞ ወደየት ይሄድ ይሆን? ምን ይፈጠር ይሆን?
በቀጣዩ ጦማር እንመለከታለን። ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን።) ወስብሐት ለእግዚአብሔር። ይቆየን።
©ዘዲያቆን መልአኩ ይፍሩ
ጥቅምት 23/ 2010 ዓ.ም
ጎንደር/
ኢትዮጵያ
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ