በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
(በዲያቆን መልአኩ ይፍሩ ዘውሉደ ብርሃን)
በቀደመው ክፍል ላይ ደቀ መዝሙር ማለት ማለት እንደኾነ እና ደቀመዝሙርን እውነተኛ ደቀ መዝሙር የሚያደኙትን
ነገሮች መመልከት ጀምረን ነበር። ደቀ መዝሙር እውነተኛ የኾነ ዋጋን ለማግኘት እና እውነተኛ ደቀመዝሙር ከኾነ የተወዳጁን መምህሩን
ቤት ጠብቆ የሚያስጠብቅ፣ አክብሮም የሚያስከብር እንደኾነ፤ እኛም የኹላችን መምህር መድኅን ዓለም ክርስቶስ የከፈለልንን ዋጋ ተመልክተን
ሕንጻ መንፈስ ቅዱስ የኾነውን ሰውነታችንን በንስሐ እያነጻን በስጋወደሙ ማደስ እንደሚገባን፣ ክርስቶስ ውድ ዋጋ የከፈለባትን ሰማእታት
መራራ ሞትን የታገሱላትን ቤተክርስቲያን እጅግ በጥንቃቄ እንድንጠብቃት ያስፈልጋል።
v የመምህሩን እና የቀድሞ ርቱዓን ደቀመዛሙርትን አሠረ ፍኖት መከተል እና እነርሱን መምሰል አለበት።
o በዚህች ምድራዊት ገነት እንደኾነች
ሀገራችን ውስጥ በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ለብዙ ዘመናት ሲሰጥ የቆየው የአብነት ትምህርት ወደዚህ ትውልድ የደረሰው
በቅዱሳኑ ጸሎት እና በደቀመዛሙርቱ ትጋት፣ የቀደሙ መምህራኖቻቸውን አሠረ ፍኖት በመከተላቸው ነው። ደቀ መዝሙር የመምህሩን እና
የቀደሙትን ርቱዓን ደቀመዛሙርት አሠረ ፍኖት በትክክል የሚከተል እና እነርሱን የሚመስላቸው ከኾነ የመምህሩን ትምህርት በነበረበት
አጽንቶ ማስቀጠል ይችላል።
o ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ኤልሳዕን
ስንመለከተው፣ የመምህሩን አሠረ ፍኖት በሚገባ ሲከተል እና መምህሩን ሲመስለው እናገኛለን። እንደውም በሚገርም ኹኔታ መምህሩ ከርሱ
በሚለይበት ወቅት የለመነው ነገር የመምህሩ ጸጋ በርሱ ላይ እጥፍ ኹኖለት እንዲያድርበት እና የርሱን መንገድ እንዲያስቀጥል ነበር። ከ ዚህም የተነሳ መምህሩ ቅዱስ ኤልያስ
“ትልቅ ነገር ለምነሃል። ነገር ግን ከአንተ በምወሰድበት ጊዜ ብትመለከት ይኾንልሃል” ነበር ያለው።
o ቅዱስ ኤልሳዕም ይኽን አምኖ እንደተባለው
አደረገና የቅዱስ ኤልያስን በጎናጸፊያ ተቀብሎ ኤልያስ ከፍሎት ያለፈውን ባህረ ዮርዳኖስ በስሙ ከፈለው። ኤልያስ አንስ ሙት ሲያስነሳ
ኤልሳዕ ግን ኹለት ሙት ነበር ያስነሳው። የመጀመሪያውን መሕይወተ ሥጋ ሳለ ሲኾን ሌላኛውን ግን የሞተውን ሰው ሊቀብሩት ከጉድጓድ
ሲያስገቡት በዚያ ጉድጓድ የነበረው የኤልሳዕ አጽም በነካው ጊዜ ወዲያውኑ ተነስቷል።ነቢየ እግዚአብሔር ለእግዚአብሄር ይቀና እንደነበር
ኹሉ ቅዱስ ኤልሳዕም ፍጹም ቀናተኛ ነበረ። ቅዱስ ኤልያስ ለእውነት ሲል እንደተሰደደ ኹሉ ቅዱስ ኤልሳዕም ፍጹም እውነትን ለማጽናት
የተጋ ቅዱስ ነበር።
o እውነተኛው መምህር ኢየሱስ ክርስቶስ
በመዋእለ ሥጋዌው ሲመላለስ ኃጢአተኞችን ሳይጸየፋቸው ከነርሱ ጋር እያሳለፈ
ወደ ሕይወት ይጠራቸውና ያድናቸው፣ ለመንግስቱም ምስክር ያደጋቸው ነበር። በዚህም የተነሳ እነዚያ በሰዉ ኹሉ ሰንድ ይጠሉ
የነበሩ ልባቸው በክርስቶ ስ ፍቅር እየነደደ ሳይሳሱ ሥጋቸውን ለሞት፣ ለእሳት፣ የአውሬ ይሰጡ ነበር። በዚህም ክርስቶ ስን መስለውታል።
ደቀ መዝሙር መምህሩን ከመሰለ፣ መምህሩን የሚያስደስቱን ነገሮች ለማድረግ የግድ የመምህሩን ትእዛዝና የመምህሩን ከአጠገቡ መኖር
አይጠብቅም። በኼደበት እና በኖረበት ቦታ ኹሉ እንደመምህሩ የቀና አነዋወርን ለመኖ ር የተጋ ይኾናል። መጽሐፍ በጊዜውም ያለጊዜውም
ጽና የለው ለዚሁ ነው።
o መምህራችን ኢየሱስ ክርስቶስን መምህራችን
ነህ ካልነው እና እኛም ለክርስቶስ ደቀመዛሙርቱ እንባል ዘንድ እርሱን መምሰል ይጠበቅብናል። እርሱ የወደዳቸውን ኹሉ መውደድ፤ እንርሱ
የሚደሰትበትን በጊዜውም ኾነ አለጊዜው ለማድረግ መትጋት ይጠበቅብናል። ቅዱስ ጳውሎስ በመልእክቱ ሲነግረን
“እኔ ክርስቶስን እንደምመስል እኔን
ምሰሉ።” /1ኛ ቆሮ11፥1 / በማለት ነግሮናል። ክርስቶስን መምሰል
ማለት በግብር ነው። እርሱ ያደረገውን ማድረግ። ጌታችን ቀን በትጋት ሲያስተምር ከዋለ በኋላ ምሽቱን በጸሎት ያሳልፋ። እውን ይኽን
የሚያደርገው ከዚያ ጸሎት የሚጠቀመው ነገር ኑሮ ይኾን? አይደለም። ዳሩ ግን እኛ እርሱን አብነት አድርገን እንደርሱ በጸሎት የጸና
የተጋ ሕይወት እንዲኖረ ን ለማስተማር እንጂ እርሱማ ስጡኝ አይል ሰጭ፣እከብር አይል ክቡር፣ የማይነጥፍበት ባዕል ነው። ፈጣሬ ዓለማትን
ያደረገውን ተመ ልክተን በሕይወት በመተርጎም ደቀ መዝሙርነታችንን በሥራ በመግለጥ ምስክርነታችንን እውነት ለማድረግ ከአኹኑ መጀመር
ይገባናል። ለዚህም የቅዱሳኑ ኹሉ ጸሎት እና የወላዲተ አምላክ አማላጅነት
ይርዳን። አሜን።
v መምህሩ ለሚሰጠው እና ለቆመበት ዓላማ ሳያወላውል ጸንቶ መቆም ይገባዋል
o ደቀ መዝሙር አስቀድመን እንደተናገርነው መምህሩን መስሎ ነው የሚኖረው። ስለዚህም በመምህሩ መንገድ
እስከተጓዘ ድረስ መምህሩን ያገኙት ነገሮች ኹሉ፣ ከዚያም በላይ የኾኑ ነገሮች ስለሚገጥሙት ለዚያ ባለመሸነፉ በዓላማ ጽናት መቆም
ይገባዋል። በዓላማ ጽናት መቆም ተብሎ ሲነገር እንደቀላል የምናስበው ነገር እንዳልኾነ ልብ ልንል ያስፈልጋል።
o መድኅን ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ስለዚህ
ነገር ሲነግረን ቅዱሳን ሐዋርያትን “እንደበጎች በተኲላ መኻከል እልካችኋለሁ” ብሎ ተናግሯል። ይኽን የነገራቸው በሚጓዙበት ጎዳና
ላይ የሚገጥማቸውን ነገር ኹሉ ተመልክተው ከዓላማቸው ጽናት እንዳይታጎሉ ለማስተማር ነው። ደቀ መዝሙር ኹልጊዜም የሚገጥመውን ፈተና
እንደትምህርት ቤት በመቊጠር ወደዓላማው በፍጥነት የሙጓዝ ነው።
§ ይኽን በደንብ እንድናስብበት የሚያደርገንን
ምሴተ ሐሙስን ማስታወስ ያስፈልጋል። በምሴተ ሐሙስ ጌታችን ተግቶ እየጸለየ ተጨንቆ ሳለ ደቀመዛሙርቱ ግን ተኝተው ነበር። እርሱም
ቀሰቀሳቸውና “ወደፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸልዩ፣ የሰው ልጅ ተላልፎ ይሰጥ ዘንድ ሰዓቱ ደርሷል” ካላቸው በኋላ ወዲያውኑ ይሁዳ
ከወታደሮችና ከፈሪሳውያን ጋር መጣ። ካንተ አልለይም እያለ በእመነት ይናገር የነበረው ጴጥሮስን ጨምሮ ኹሉም ቢኾኑ ከፍቊረ እግዚኧእ
ቅዱስ ዮሐንስ በቀር ጸንቶ ለሽልማት የበቃ አልተገኘም። ፍቊረ እግዚእም
መከራ መስቀሉን በመመልከቱ የተነሳ እድሜ ዘመኑን በሐዘን ተዘብሮ ስለኖረ ቊጾረ ገጽ በመባልም ተጠርቷል። እንደቅዱስ ዮሐንስ ፍቊረ
እግዚእ ውድ የኾነችውን ስጦታ ለመሸለም እስከ ዓላማ ድረስ መታገስ እና መጽናት ያስፈልጋል። ለዚህም የቅዱሳኑ ኹሉ እና የድንግል
ማርያም ጸሎት አይለየን።በቀጣዩ ክፍል የቀሩትን ነገሮች እንመለከታለን። ይቆየን።ይቀጥላል።
©ዘዲያቆን መልአኩ ይፍሩ
ኅዳር 21/ 2010 ዓ.ም
ጎንደር/ ኢትዮጵያ
©ዘዲያቆን መልአኩ ይፍሩ
ኅዳር 21/ 2010 ዓ.ም
ጎንደር/ ኢትዮጵያ
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ