ከዚያ ወዲያ
ኢየሱስ ከዲያብሎስ ይፈተን ዘንድ መንፈስ ወደ ምድረ በዳ ወሰደው፥
ማቴ4፡1
ቅዱስ
ማቴዎስ ይህንን የጌታችንን የመጾሙን ነገር መጻፍ ሲጀምር ከዚያ ወዲያ ብሎ ይጀምራል።ለምን እንዲህ በማለት ጀመረ ቢሉ አመክንዮውን
ከዚህ ይናገሩታል።አስቀድሞ በምእራፍ ሦስት ላይ መንፈስ ቅዱ በርግብ አምሳል እንደወረደ እና ከደመናም የምወደው በርሱ ደስ የሚለኝ ልጄ ይህ ነው
እንደተባለ ተናግሯልና ይህ ከሆነ በኋላ ተጠምቆም ከወጣ በኋላ ሳይውል ሳያድር እለቱን መሄዱን ለመናገር ነው።
መንፈስ
ወሰደው ማለቱ እንደምን ነው ያሉ እንደሆን መንፈስ ያላት የገዛ ፈቃዱ ናት
(ወሶበ ትሰምእ እንዘ ይብለከ ወሰዶ ገዳመ ኢትሐሊኬ ከመ ፍጡርውእቱ አላ መንፈስሰ ሥምረቱ ይእቲ_ገዳም ወሰደው ሲል በሰማህ ጊዜ ፍጡር እንደሆነ አታስብ መንፈስ ያለው የገዛ ፈቃዱ
በጎ ፈቃዱ ነው እንጂ።)እንዲል
።ዳግመኛም መንፈስ ብሎ መንፈስ ቅዱስ የሚል አብነት ያመጣል።ይህስ ሰማእታትን ለደም
ጻድቃንን ለገዳም እንደሚያነሳሳቸው አነሳሳው ማለት እንዳይደለ ልብ
ይሏል። በፈቃድ አንድ መሆናቸውን መናገር ነው እንጂ።
ቅዱስ
ዮሐንስ አፈወርቅ የማቴዎስን ወንኤል በተረጎመበት ትምህርቱ በ13ኛው ክፍለ ትምህርት ላይ ጌታችን ይፈተን
ዘንድ የፈቀደበትን አመክንዮ እንዲህ ገንጾልናል።
ለእኛ
አብነት ይሆነን ዘንድ ሁሉን አድርጎ አሳየን።ወደዚያ ምድረበዳ ሄዶ
ይፈተን ዘንድ ጸንቶ ሂዷል።ስለዚህም የተጠመቀ በኋላ ታላላቅ ፈተናዎችን በጽናት ይቋቋም ዘንድ እንዳለው ለመናገር።
ስለዚህ
ክንዶች ተሰጠተውሃልትሰንፍ ዘንድ ሳይሆን ትፈተን ዘንድ ነው እንጂ።ስለዚህ ምክንያት ፈጣሪ ፈተናዎቹ በመጡ ግዜ አልከለከላቸውም
ነበር።
1. አንተ
እጅግ ጠንካራ እንደሆንህ ለማስተማር
2. ዳግመኛም
ታላቅ ጸጋ ቢሰጠን እንኳን በዚያ እንዳትመካ በትሐትና እንድትኖር እኒህ ፈተናዎች አንተን እንዲህ እንድትኖር በኃይላቸው ያደርጉሃል
3. ክፉው
ዲያብሎስ ለጊዜው እርሱን እንደካድህ ቢጠራጠርም ከነዚህ አርእስተ
ኃጣውእ የተነሳ ፈጽሞ እንደተውከው እና ከርሱም እንደተለየህ እርግጥ ይሆንለታልና
4. ዳግመኛም
ስለዚህ ምክንያት አንተ ብርቱ እና ጠንካራ ትሆን ዘንድ ከብረትም ሁሉ የጠነከርህ ትሆን ዘንድ
5. አምስተኛም
ስለተዘጋጀልህ አብት(ስጦታ)ግልጽ
የሆነ እማሬ ታገኝ ዘንድ ነው።
ዲያብሎስ አንተ ከፍ ወዳለ ክብር ተወስደህ
ካላየ በቀር በኃይል አያጠቃህምና።ይህም ይታወቅ ዘንድ ለምሳሌ ገና ከጅምሩ አዳምን የፈተነው ታላቅ የሆነውን የተሰጠውን ክብር ተመልክቶ
ነው።ዳግመኛም ስለዚሁ ምክንያት ሲከበርና በሁሉ አምላክ ዘንድ ሲከበር
ተመልክቷልና እዮብን ተቃውሞ በርሱ ላይ ተነሳሳበት።
ጌታም “ወደፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸልዩ” ማለቱስ እንደምን ነው ትለኝ እንደሆን ጌታ እንዲሁ ሲሄድ አላየህም ዳሩ ግን ተወሰደ ይላልና። በዚህም እኛ ዘለን
ወደፈተና መግባት እንደሌለብን ዳሩ ግን ልንወሰድ እንደምንችል ሲያስተምረን ነው።
ይቆየን!
© መላኩ
ዘውሉደ ብርሃን
11-06-2009 ዓም
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ