በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
" በቀትርም ጊዜ እርሱ በድንኳኑ ደጃፍ ተቀምጦ ሳለ እግዚአብሔር በመምሬ የአድባር ዛፍ ተገለጠለት።"
(ኦሪት ዘፍጥረት 18:1)
በወርኃ ሐምሌ በሰባተኛው እለት ከምንዘክራቸው በዓላት መካከል አንዱ ቅድስት ሥላሴ በአብርሃም ቤት የተገለጡበት በዓል ነው። ይህን በዓል ስናከብር የምናስታውሳቸው ዋና ዋና ጉዳዮች አሉ። እሊህም ÷
+እግዚአብሔር ለአብርሃም የሰጠው የጥምቀት ምሳሌ ግዝረት
+ የሥላሴ በአንድነት እና በሦስትነት ለአብርሃም መገለጥ
+የቅዱሳንን ምልጃ በአጸደ ሥጋ፣ እግዜብሔር ቅዱሳኑን ምንያህል እንደሚወድ እና የሰጣቸውን ቃልኪዳን እንደሚያከብር
እግዚአብሔር አብርሃምን ከመጥራቱ በፊት አብርሃም ጣዖት በመሸጥ ይኖር እንደነበር ቅዱሳት መጻሕፍት ይነግሩናል።
አብርሃምም የጣዖታቱን ደካማነት ተመልክቶ ሰባብሮ ከጣለ በኋላ ፈጣሪውን ፍለጋ ወጥቷል። እጅግ ብዙ የደከመ ቢሆንም
ግን አብርሃም እግዚአብሔርን በድካሙ ብዛት ሊያገኘው አልቻለም ነበር።
ከዚህ
በኋላ አብርሃም "አምላከ ፀሐይ ተናበበኒ-የፀሐይ አምላክ አነጋግረኝ" ብሎ በፊጹም መሻት ቢለምን እግዚአብሔር
አነጋገረው። ከወገኖቹም ተለይቶ ይወጣ እና እርሱ ወደ ሚያሳየው ምድር ይሄድ ዘንድ ሲያዘው ምንም ሳያቅማማ ወጣ።
በዚህም የተነሳ እግዜብሔር ከአብርሃም ጋር ቃልኪዳንን አደረገ። ዘሩንም እንደምድር አሽዋ እንደሰማይ ክዋክብት
እንደሚያበዛለት ቃልኪዳንን ሰጠው።
አብርሃምም
ድንኳን ሠርቶ በተመሳቀለ መንገድ እንግዳ እየተቀበለ ሲኖር የመልካም ሥራ ጠላት የሆነው ዲያብሎስ እጅግ የተጎዳ
መንገደኛ መስሎ በመገለጥ ጉዳቱንም አብርሃም እንዳደረሰበት አድርጎ በመናገር እንግዶቹን አስቀረበት። አብርሃምም
እንግዳ ባለማግኛቱ ሳይበላ ለሦስት ቀን ቆየ። እግዚአብሔርም ለዲያብሎስ ዘለፋ፣ ለአብርሃም ደግሞ ክብርና ፍቅር ሲል
በቀትር በመምሬ የአድባር ዛፍ ሥር ተገለጠለት። በሦስት ሽማግሌዎች አምሳል።
አብርሃምም
አንድ ጊዜ ጌታዬ አንድ ጊዜ ደግሞ ጌቶች እያለ በብዙና በአንድ እያደረገ ሲጠራቸው እንመለከታለን። ለሚስቱም ሦስት
መስፈሪያ ዱቄት በአንድ እንድትለውስ ነግሯት ነበር። ይህም የሥላሴን አንድነትና ሦስትነት የሚገልጥ ድንቅ አነጋገር
ነው።
ከዚህ
በኋላም እግዜብሔር በዓመቱ ተመልሶ እንደሚመጣ ሣራም እንደምትወልድ ነገረው። ደም ቆርጣ አርጅታ ስለነበር ሳቀች።
ስለዚህም ልጇን ይስሐቅ እንደምትለው ነገራት። እግዜአብሔር ከዚህ ወጥቶ ወደ ሰዶም ባቀና ጊዜ ለአብርሃም
የሚያደርገውን ነግሮት ነበር።
" እግዚአብሔርም አለ። እኔ የማደርገውን ከአብርሃም እሰውራለሁን? "
(ኦሪት ዘፍጥረት 18:17)
አብርሃምን ስለሚያደርገው መንገር ለምን አስፈለገው??? መልሱ የአብርሃምን ክብር ለመግለጥና ስለነዚያ ሕዝቦች ማርልኝ ብሎ ይለምነው ዘንድ ነው።
ልክ በመጽሐፈ እዮብ ላይ እነዚያን የእዮብን ወዳጆች እዮብ እንዲማልድላቸው እንደመራቸው። ምክንያቱም ቅዱሳን ሲማልዱ፣
+ የሚማለድለት ሰው ወደ ቅዱሳኑ መጥቶ ሲለምን ይማልዳሉ
+ እግዚአብሔር ራሱ የሚማለድለትን ሰው ወደ ቅዱሳኑ ይመራዋል(መጽሐፈ እዮብ)
+ ከፍጹም ርኅራኄያቸው የተነሳ ይማልዳሉ (እንደ ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ፣ እንደእመቤታችን ለበላኤ ሰብዕ)
አንዳንዶች ግን እንዲህ ስለምልጃ ሲነገር እግዚአብሔርን ርኅራኄ አልባ፡ ቅዱሳንን ደግሞ ርኅሩኃን ማድረግ
ይመስላቸዋል ልቦና ይስጣቸው። ዳሩ ግን ይህም(ምልጃም) ቢሆን የእግዚአብሔርን የርኅራኄውን ብዛት የምናይበት ነው።
በዚያውም ላይ እንዲጸልዩልን የሚያደርጋቸውና ቃልኪዳንም የሚሰጣቸው ርሱ እግዚአብሔር ነው።
አብርሃም
ለምልጃ በቆመ ጊዜ በሚያቀርባቸው ነገሮች ሁሉ እግዚአብሔር አብርሃም የጠየቀው የቅዱሳን ብዛት ቢገኙ ሀገሪቱን
እንደሚምር ነግሮት ነበር። ከሃምሳ ቅዱሳን አንስቶ እስከ አስር ቅዱሳን ድረስ ለምኖት ነበር። (ዘፍ18፥23-33)
" ይህ ከአንተ ይራቅ፤ ጻድቁን ከኃጢአተኛ ጋር ትገድል ዘንድ፥ ጻድቁም እንደ ኃጢአተኛ ይሆን ዘንድ፥ እንደዚህ ያለው አድራጎት ከአንተ ይራቅ። የምድር ሁሉ ፈራጅ በቅን ፍርድ አይፈርድምን?"
(ኦሪት ዘፍጥረት 18:25)
እግዚአብሔር
አብርሃምን ለቃልኪዳኑ ምልክት ይሆን ዘንድ የአብርሃም ወገን የሆኑት ሁሉ እንዲገዘሩ ነግሮታል። በዚህም ምልክትነት
ሕዝብ ከአሕዛብ፣ ግዙራን ከቆላፋን ይለዩ ነበር። ይህም ለሐዲስ ኪዳኑ ጥምቀት ምሳሌ ነው። በጥምቀት አማኒው
ከኢአማኒው እንዲለይ።
ስለዚህም ይህን በዓል ስናከብር እሊህን ዐበይት ነገሮች በማሰብ ይሆን ዘንድ ይገባል። አምላከ ቅዱሳን እንደ አብርሃም ያሉ ደጋግ አበውን ያቆይልን።
የቅዱሳኑ ሁሉ እና የድንግል ማርያም ጸሎት አይለየን አሜን።
ሥዕለ አድኅኖ መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ገጽ
©ዲ/ን መላኩ ይፍሩ
ሐምሌ 6/ 2009 ዓ/ም
አዲስ አበባ
" በቀትርም ጊዜ እርሱ በድንኳኑ ደጃፍ ተቀምጦ ሳለ እግዚአብሔር በመምሬ የአድባር ዛፍ ተገለጠለት።"
(ኦሪት ዘፍጥረት 18:1)
በወርኃ ሐምሌ በሰባተኛው እለት ከምንዘክራቸው በዓላት መካከል አንዱ ቅድስት ሥላሴ በአብርሃም ቤት የተገለጡበት በዓል ነው። ይህን በዓል ስናከብር የምናስታውሳቸው ዋና ዋና ጉዳዮች አሉ። እሊህም ÷
+እግዚአብሔር ለአብርሃም የሰጠው የጥምቀት ምሳሌ ግዝረት
+ የሥላሴ በአንድነት እና በሦስትነት ለአብርሃም መገለጥ
+የቅዱሳንን ምልጃ በአጸደ ሥጋ፣ እግዜብሔር ቅዱሳኑን ምንያህል እንደሚወድ እና የሰጣቸውን ቃልኪዳን እንደሚያከብር

" እግዚአብሔርም አለ። እኔ የማደርገውን ከአብርሃም እሰውራለሁን? "
(ኦሪት ዘፍጥረት 18:17)
አብርሃምን ስለሚያደርገው መንገር ለምን አስፈለገው??? መልሱ የአብርሃምን ክብር ለመግለጥና ስለነዚያ ሕዝቦች ማርልኝ ብሎ ይለምነው ዘንድ ነው።
ልክ በመጽሐፈ እዮብ ላይ እነዚያን የእዮብን ወዳጆች እዮብ እንዲማልድላቸው እንደመራቸው። ምክንያቱም ቅዱሳን ሲማልዱ፣
+ የሚማለድለት ሰው ወደ ቅዱሳኑ መጥቶ ሲለምን ይማልዳሉ
+ እግዚአብሔር ራሱ የሚማለድለትን ሰው ወደ ቅዱሳኑ ይመራዋል(መጽሐፈ እዮብ)
+ ከፍጹም ርኅራኄያቸው የተነሳ ይማልዳሉ (እንደ ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ፣ እንደእመቤታችን ለበላኤ ሰብዕ)

" ይህ ከአንተ ይራቅ፤ ጻድቁን ከኃጢአተኛ ጋር ትገድል ዘንድ፥ ጻድቁም እንደ ኃጢአተኛ ይሆን ዘንድ፥ እንደዚህ ያለው አድራጎት ከአንተ ይራቅ። የምድር ሁሉ ፈራጅ በቅን ፍርድ አይፈርድምን?"
(ኦሪት ዘፍጥረት 18:25)

ስለዚህም ይህን በዓል ስናከብር እሊህን ዐበይት ነገሮች በማሰብ ይሆን ዘንድ ይገባል። አምላከ ቅዱሳን እንደ አብርሃም ያሉ ደጋግ አበውን ያቆይልን።
የቅዱሳኑ ሁሉ እና የድንግል ማርያም ጸሎት አይለየን አሜን።
ሥዕለ አድኅኖ መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ገጽ
©ዲ/ን መላኩ ይፍሩ
ሐምሌ 6/ 2009 ዓ/ም
አዲስ አበባ
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ