ቅዳሜ 19 ጃንዋሪ 2019

❤በእንተ ጥምቀት (On Baptism No.1)❤ ቅዱስ ቄርሎስ ዘኢየሩሳሌም

  ❤"ወይስ ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ የተጠመቅን ሁላችን ከሞቱ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ እንደ ተጠመቅን አታውቁምን? እንግዲህ ክርስቶስ በአብ ክብር ከሙታን እንደ ተነሣ እንዲሁ እኛም በአዲስ ሕይወት እንድንመላለስ፥ ከሞቱ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ በጥምቀት ከእርሱ ጋር ተቀበርን።" /ሮሜ ፮፥፫-፬/

   ❤ በሂሶጵ ለሚረጩትና በመንፈሳዊውም ሂሶጵ ለሚጸሩት (ንጹሕ ለሚሆኑት) ለነርሱ በመከራው መጠጥ /ሀሞትና መጻጻ ሲጠጣ ለማለት ነው/ ጊዜ በሂሶጵ እና በዘንጉ ኃይሉ ተሰጥቷቸዋልና ስለዚህ ሰማያት ደስ ይበላችሁ ምድርም ሐሴትን አድርጊ። የሰማይ ሠራዊትም ደስ እየተሰኙ ሳለ ከመንፈሳዊው ሙሽራ ጋር ኅብረት ሊያደርጉ (ሊዋሐዱ) ያሉት ነፍሳትም የተዘጋጁ ይሁኑ፣ የጌታን መንገድ አስተካክሉ እያለ በምድረ በዳ የሚጮኽ አንድ ድምጽ ተሰምቷልና። /ኢሳ ፶፥፫/ ይኸውም ደግሞ ቀሊል ነገር ወይም ተራ ነገር እና እንደሥጋ (ፈቃድ) ያለ' ኅብረት (አንድነት) አይደለም ነገር ግን በእምነት መሠረት የተደረገ የሐሳሴ ኲሉ (All-searching) መንፈስ ምርጫ ነው እንጂ። ጋብቻ እና የዚህ ዓለም ቀጠሮ በፍርድ (በውሳኔ) በፍጹም አልተደረጉምና ነገር ግን ሀብት አሊያም ውበት ባለ' ጊዜ ሁሉ በዚያ ሙሽራው ይገኛል፤ ነገር ግን እዚህ ላይ የአካል ውበት (ሥነ ላህይ)ን አይደለም የነፍስን ንጹሕ ሕሊና እንጂ፤ የተወገዘውን ገንዘብም አይደለም ነገር ግን በነፍስ ያለ'ውን የአምልኮ ገንዘብ (ጸጋ) ነው እንጂ።

        (Source: -from Catachethical lectures)
        ትርጉም፥ ዲያቆን መልአኩ
        ጥር ፲፣ ፳፻ ወ፲፩  ዓ.ም
         ሲቹዋን ቸንዱ፣ ቻይና