ዲያቆን መልአኩ ይፍሩ ዘውሉደ ብርሃን:
" አሐቲ ይእቲ ለእማ ወኅሪት ይእቲ ለእንተ ወለደታ -
ለእናቷ አንዲት ናት ለወለደቻትም የተመረጠች ናት "
መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን
" ኦ ማርያም አኮ በፍትወተ ደነስ ዘአጸለስኪ አላ በሩካቤ ዘበሕግ እም ሐና ወኢያቄም ተወለድኪ
- ማርያም ሆይ በኃጢአት በሆነ ፍትወት የተጸነሽ አይደለም በሕግ በሆነ ሩካቤ ከኢያቄም ከሐና ተወለድሽ እንጂ "
ቅዱስ ሕርያቆስ
" ወኮንኪ ለነ ተንከተመ ለዕርገት ውስተ ሰማይ - ከምድር ወደ ሰማይ ለመውጣት መሰላል ሆንሽን "
ቅዱስ ኤፍሬም
" መሠረታቲሃ ውስተ አድባር ቅዱሳን
ያበድሮን እግዚአብሔር ለአናቅጸ ጽዮን
እም ኲሉ ተአይኒሁ ለያእቆብ
መሠረቶቿ በተቀደሱ ተራሮች ነው
ከያእቆብ ከተማ ሁሉ እግዚአብሔር የጽዮንን ደጆች መርጧልና "
ቅዱስ ዳዊት
" ማርያምሰ ተኀቱ ውስተ ከርሱ ለአዳም ከመ ባህርይ ጸአዳ - ማርያምማ በአዳም ባህርይ ውስጥ እንደ ነጭ(ጸአዳ እንቊ) ታበራ ነበር "
ቅዱስ ያሬድ