በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
(በዲያቆን መልአኩ ይፍሩ ዘውሉደ ብርሃን)
በቀደመው ክፍል ላይ ደቀ መዝሙር የመምህሩንና የቀደሙትን ርቱዓን ደቀ መዛሙርት አሠረ ፍኖት መከተልና
እነርሱን መምሰል እንዳለበት፣ በዚህም ስር ሌሎችን ነገሮችን አንስተን ተመልክተን ነበር። ለዛሬ ደግሞ የቀሩትን እንመለከታለን።
ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን።
v ከመምህሩ ጎዳና የሚያስወጡትን ድምጾች ኹሉ ከመስማት ዠሮውን መዝጋት አለበት
o ደቀ መዝሙር በመምህሩ ጎዳና ጸንቶ
ተጉዞ ሽልማቱን ለመቀበል፣ ከመምህሩ ጎዳና አስወጥተው የሚያስጉዙትን ማናቸውንም ድምጾች መስማትን መተው አለበት። በመልካም ጎዳና
እየተጓዘ እስካለ ድረስ ደቀ መዝሙር ምንጊዜም ቢኾን የመልካም ነገር
ጠላት የኾኑት ኹሉ እርሱን ለማስወጣት እንደተጉ መኾናቸውን ማስተዋል አለበት። በመጽሐፍ እንደተባለ “መንፈስን ኹሉ አትመኑ”፣ መንፈሳት
ቅዱትን መስለው ርኩሳት መናፍስት ሊመጡ ይችላሉ እና በማስተዋል ሊጓዝ ይገባል።
o ቅዱስ ዳዊትም በመዝሙሩ እንደተናገረው
“ብጹእ ብእሲ ዘኢሖረ በምክረ ረሲዓን_ በክፉዎስ ምክር ያልኼደ ምስጉን ነው” እንዳለው ደቀ መዝሙርነቱ በትጋት ከመልካም ዋጋ ጋር
ለመፈጸም ማስተዋል ይገባዋል። “ክፉ ባልንጀርነት መልካሙን ጠባይ ያጠፋዋልና ከማያምኑ ጋር በማይመች አካኼድ አትኺድ”። መጽሐፉ
በማይመች አካኼድ አትኺድ አለ እንጂ ከማያምኑ ጋር ፍጹም አትገናኝ አላለም። በማይመች አካኼድ ማለት ምን ማለት ነው?
§ የሚያስተምሩንን ክኽደት እና ኢክርስቲያናዊ
ጠባይ መቀበል
§ ወደሚያመልኩበት ቦታ አብሮ ኼዶ መሳተፍ
§ በምን ችግር አለው የሚነግሩንን ትንሽ
የሚመስል ምግባረ ሃይማኖት መተው(ምሳሌ፦ ጾምን መተው፣ የኢአማንያንን
የአምልኮ ሥርዓት መሳተፍ፣ጸሎትን ከመጭራሹ መተው፣ ኢክርስትያናዊ ጸያፍ ትእይንቶችን መሳተፍ) እና የመሰሉትን ማድረግ የማይመች
ተብለው በቅዱስ መጽሐፍ የተገለጡ ናቸው።
o በዚህ አካኼዱ ላይ ደቀ መዝሙር መጠንቀቅ
ካልቻለ በሰይጣን ወጥመድ እንደ ቅዱስ ሙሴ ባሕታዊ ተይዞ ይወድቃልና ሊጠነቀቅ ይገባዋል።
§ ቅዱስ ሙሴ ባሕታዊ ከመምህሩ ጋር ሲኖር
መምህሩ ኹልጊዜም በበረሐ ስለሚኖሩት አበው ክብር እና ተጋድሎ ይነግሩት ስለነበር ልቡ በበረሐው ሕይወት ተመስጦ ነበርና እርሳቸው
ካረፉ በኋላ ከዚያ ወደበረሐ ወጣ። በዚያም ለብዙ ዓመታት ከኖረ በኋላ አሸናፊነት ስሜት ሲሰማው ሰይጣን ከቀደሙት አበው አንዱን
ተመስሎ በርቀት ከሙሴ በአት እየራቀ ይኼዳል። ሙሴም ይኽን ሲመለከት፣ በልቡ ማሰብ ይጀምራል ሰይጣንም ቀስእያለ በሙሰ ልብ ውስጥ
ሐሳብ መፈጠሩን ስለተመለከተ ተጠግቶ አጠገቡ ይቀመጣል። ነገር ግን አያናግረውም ነበር። ልክ ሙሴ ለጸሎት ሲቆም ትቶት ይኼዳል፣
ሲጨርስ ደግሞ መጥቶ አጠገቡ ይቀመጣል፤ ግን አያናግረውም ነበር። ሙሴ መጠርጠር ቢኖርበትም እርሱ ግን ያሰበው “እኔ ከቀደሙ አባቶች
ጋር ጸሎት ማድረግ የተገባኝ ባልኾን ነው”ብሎ ነበር።
§ ሰይጣንም በሙሴ ልብ ውስጥ ሐሳብ መግባቱን
ከተመለከተ በኋላ ማናገር ጀመረው። ታሪኩን ነገረው እንዴት ካለ የዝሙት ኃጢአት እግዚአብሔር አውጥቶ ከዚህ ክብር እንዳደረሰው።
እንዴት ያለ ሀብታም እንደኾነ እና ዛሬም የመጣው እረፍቱ ስለደረሰ ሙሴ እንደሚቀብረው ተነግሮት እንደኾነ ነገረው። ሙሴም በሙሉ
ልቡ አመነው።
§ በበነጋው ተያይዘው ወደዚያ አባት
(ሰይጣን) መኖሪያ በአት ተጓዙ። ከብዙ ድካም በኋላ ከአንድ ቤተመንግስት ከመሰለ ቤት ደረሱ። ያም ሰው ሙሴን “እንግዲህ ቤቴ ይኼ
ነው። እንደምታየው እንደነገርኹህም ሀብታም ነኝ፤ አንተም የምትቀብረኝ በዚሁ ቦታ ነው። ” ይለውና አብረው ወደ ውስጥ ሲገቡ የሰው
ጥላ ይ"መለከትና “ምንድነው ይኼ? በዚህ ቦታ ሌላ ሰው አለ እንዴ?” ብሎ ሲጠይቅ “ቀድሞ ዘማዊ በነበርሁበት ጊዜ የወለድኋት
ልጄ ናት። እናቷ አኹን ከእግዚአብሔር ጋር ስለኾንህ አሳድጋት ብላኝ ነው። እኔን ከቀበርህ በኋላም እርሷን አግብተኽ ነው የምትኖረው”
በማለት ይመልስለታል። ልብ አድርጉ ከበአቱ ካስወጣው በኋላ እንዴት እያለሳለሰ እየጣለው እንደኾነ። ሙሴም እንዴት ይኽ ይኾናል።
እኔ መነኲሴ ነኝ። አላገባምእያለ ቢከራከረውም ተው እንጂ እንደሱ አትበል፣ ሙሴ አግብቷል፣ አብርሐምም አግብቷል፣ እዮብም አግብቷል
ሀብታምም ነበር እያለ ከኹለት ቀናት በኋላ ግን አሳመነው። ከዚያም በኋላ ኾለቱን አጋባቸውና (ሙሴን እና ሌላኛውን ሰይጣን)፣ ሙሴም
ያንን አባት (ሰይጣን) ሲሞት ቀበረው። የሰመመን እንቅልፍ መጥቶበትም ሲነቃ ያኹሉ ያየው ነገር ባዶ ነበር። ቤቱም ኾነ መቃብሩ
ሚስቱም የሉም። ሙሴም ደነገጠ። እጅግ በጣም እያዘነ ከዚህ በኋላማ ምን አደርጋለሁ ወደከተማ ልኺድና ስንቄን ይዤ መጥቼ ተጋድሎዬን
ልቀጥል ብሎ አስቦ ይኼዳል።
§ ሰይጣን ግን ብዙ እንዲያስብ ለሙሴ
እድል መስጠት አልፈለገምና ደግሞ እንደባለጸጋ ኾኖ በፈረስ ላይ ተቀምጦ
ጠበቀውና ወደየት እንደሚኼድ ጠይቆት ከርሱጋር አብረው ወደከተማው መኼድ ጀመሩ። የከተማው ጫፍ ላይ እንደደረሱም፣ ያሰውዬ ሙሴን
“በዚህ መንደር ያሉ ሰዎች ደጎች ናቸውና ከዚህ ከግንቡ ዳር ቆያቸው፣ የምትሻውን ይሰጡኻል። ሰላም ኹን” ብሎ ተሰናብቶት ኼደ።
ከዚያም አካባቢ አንዲት ሴት ወጣችና ተመለከተችው። ምን እንደሚሻም ጠየቀችው። እርሱም የሚሻው ስንቅ እንደኾነ ነገራት እርሷም ወደቤቷ አስገባችውና የሚሻውን እንዲበላ
ሰጠችው። ከጠገበም በኋላ ሲጨዋወቱ ስለሕይወቱ ሲነግራት እርሷም መልሳ “አኹንኮ አግብተሃል፣ እኔን ደግሞ እንደምታየኝ ብጨኛ ነኝ፣
አግባኝ” አለችው። እርሱም እንደዚያ ከኾነማ ምን ገዶኝ ይልና ይስማማል። እየተጨዋወቱ ውድቅት ሲያልፍ በልጅቷ እየተሳበ መምጣቱን
ተረዳችና “እንግዲህ እኔን ለማግባት የምትፈልግ ከኾነ አይኹድ መኾን አለብህ። ምክንያቱም እኔ ይሁዲ ነኝ። በዓለም ላይ ራሱ ያሉት
ክርስቲያኖች ይሁዲ ትክክል መኾኑ አውቀው ይሁዲ እየኾኑ ነው።” ስትለው ሙሴ ተቀበላትና አምላኩን ካደ። ልብ አድርጉ ሰይጣን እንዴት
በጥበብ አስወጥቶ እየተጫወተበት እንዳለ።
§ ከዚህ በኋላ ሲነጋ ተያይዘው ለሰው
የሰጠኹት ገንዘብ አለ ብላው ነበርና ያንን ሊያመጡ ጉዞ ጀመሩ። ከብዙ ድካም በኋላ በረሐውን እያቋረጡ ሳለ ሙሴ ደከመው። ሴቲቱ
ግን “እኔ ሴቷ እንኳ እንዲህ እየተጓዝሁ በል ተነስ ተጓዝ ” ብትለውም ደክሞትነበርና አልቻለም። ከዚያም በቅርብ ከተማ ካለ ልይ
ብላው ወደተራራ ወጣች። ከተራራውም ላይ ኹና እየጨበጨበችበት “ሙሴ እንግዲህ ዋጋ የለህም። ምንኩስናህን ጠለህ አግብተሃል። አምላክህን
ክደኸዋል። እንግዲህ ምህ ይበጅኻል? ማን ያድንሃል?” እያለ አላገጠበትነ ተሰወረው። ሙሴ ግን
በዚያ በኾነበት ነገር ኹሉ እጅጉን አዝኖ የሚገባበት ጠፋው። ምርር ብሎ እያለቀሰ እግዚአብሔር እንዲምረው እየተናዘዘ ከ15 ዓመታት
በላይ በዚያ ቆየ። ከዚያም መልአከ እግዚአብሔር ተገልጦ “ሙሴ እግዚአብሔር ንስሐህን ተቀብሏል። ከሦስት ቀናት በኋላ ታርፋለህና
ከባህታውያኑ ማኅበር አንድ ሰው ወዳንተ ነገ ይመጣል” አለው። እንደተባለውም በበነጋው አንድ ሰው ወደርሱ መጣና ወደ ማኅበረ ባሕታውያን
ወሰደው። ሙሴም በዚያ ዐጽመ ቅድሳንን ለመሳለም እንደገባ በዚያው በሰላም ዐረፈ። ልብ አድርጉ እግዚአብሔር በቸርነቱ ባይረዳው ኖሮ
ሙሴ በሰይጣን የማታለል መንገድተጉዞ አምላኩንም ክዶ ዋጋውን አጥቶ በቀረ ነበር። ስለዚህም ደቀ መዝሙር ጉዞውን በማስተዋል ማድረግ
ይገባዋል። ይቀጥላል።
©ዘዲያቆን
መልአኩ ይፍሩ ኅዳር 28/ 2010 ዓ.ም ጎንደር/ ኢትዮጵያ