አንተ ታላቅ ነህ፡ ኦ ጌታ ሆይ፡ ስለዚህም በታላቅ ሁኔታ መመስገን ይገባሃል። ታላቅስ ያንተ ኃይል
ነው ለጥበብህም ፍጻሜ የለውም። ሰውም አንተን ያመሰግንሃል፡ ያንተ እጅግ ታናሹ ፍጥረትህ የሆነው
ሰው፡ መዋቲነቱን የተሸከመው ( መዋቲነት ያለበት) ሰው፡ የኃጢአቱ ምሥክር የሆነው፡ ኩራቱን
የማትቀበለው ያ ምስክር፡ ያ ሰው አንተን ያመሰግንሃል፡ ዳሩ ግን ያንተ እጅግ ታናሽ የሆነ ፍጡር ነው።
አንተን በማመስገን ( በአንተ ምስጋና) ደስ እንሰኝ ዘንድ ቀሰቀስከን። አንተ እኛን ለራስህ ሠርተህናልና
ልባችንም በአንተ እስኪያርፍ ድረስ ማረፊያ የለውም። ጌታ ሆይ የቱ እንዲቀድም አውቅ እና እረዳ ዘንድ
እርዳኝ፡ አንተን መጥራት ወይስ አንተን ማመን? ዳግመኛስ አንተን ማወቅ ወይስ አንተን መጥራት?
አንተን ሳያውቅህ ወደአንተ ሊጣራ የሚቻለው የለምና፡ አንተን ያላወቀህ የሆነው አንተን ባልሆንከው
መንገድ ሊጠራህ ይችላልና( ባለማወቁ ያልተገባ አጠራር እንደሚጠቀም መግለጡ ነው) ። ወይንስ
ደግሞ አንተን በመጣራት አንተን እናውቅ፡ አንተን ወደማወቅ እንመጣ ይሆን? ነገር ግን በእርሱ
ያላመኑት እርሱንም ያላወቁት እንዴት ወደርሱ ሊጣሩ ይችላሉ? እንዲሁም ጌታን የሚፈልጉት እነዚያ
ጌታን ያመሰግኑት ዘንድ ይገባል። እርሱን የሚሹት ሊያገኙት ይገባልና፡ ያገኙትም እነዚያ ሊያመሰግኑት
ይገባልና። ጌታ ሆይ፡ አንተን በመጣራት እፈልግሃለሁ፡ አንተንም በማመን ወዳንተ እጣራለሁ። አንተም
ለእኛ ተሰብከሃልና። አቤቱ ጌታ ሆይ አንተ የሰጠህኝ እምነቴ አንተን ትጣራለች፡ አንተ በልጅህ ሥጋን
መልበስ፡ በሰባኪውም አገልግሎት ቀስቅሰህኛልና።
አማርኛ ትርጉም፦ ዲያቆን መላኩ ዘውሉደ ብርሃን
ቀን 13_05_2009 ዓ.ም